በስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነይማ ሙኒር የተመራ ልዑክ በጦራ  ከተማ አስተዳደር በመንግስትና በግል ባለሀብቶች እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ምልከታ አደረጉ!!
በስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነይማ ሙኒር የተመራ ልዑክ በጦራ ከተማ አስተዳደር በመንግስትና በግል ባለሀብቶች እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ምልከታ አደረጉ!!
ነሃሴ 06/2018 :- በስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነይማ ሙኒር እና በስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሁሴን ሱነሞ የተመራ ልዑክ በጦራ ከተማ አስተዳደር በመንግስትና በግል ባለሀብቶች እየተሰራ የሚገኝ የልማት ፕሮጀክቶችን ምልከታ አድርገዋል።
የስራ ሀላፊዎቹ በከተማ አስተዳደሩ በመንግስት እየተሰራ የሚገኘው የአስፓልት ዳር ፓርክ የግንባታ ሂደት የደረሰበት ደረጃና በከተማ አስተዳደሩ በወጣት ባለሀብት አ/ላሚድ ራመቶ እየተሰራ የሚገኘውን ሸይቴየምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የደረሰበት ደረጃ ምልከታ አድርገዋል።
የስራ ሀላፊዎቹ በምልከታቸው የከተማውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የበለጠ ለማፋጠን በተቀናጀ አሰራር እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘው ግዜ እንዲጠናቀቁ የቅርብ ክትትል በማድረግ በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
የልማት ፕሮጀክቶቹ ወደ ሥራ ሲገቡ ለዜጎች የተሻለ አገልግሎት ከመስጠታቸው ባሻገር የሥራ እድል በመፍጠርና የከተማውን ኢኮኖሚ በማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱም ገልፀዋል።
በመስክ ምልከታው የጦራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ካሚል አማን፣የጦራ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ደኑር ኮሪ፣የጦራ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የገቢዎች ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚፍታ ሰብሬ፣ የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፖሎቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ዛይዳ ራመቶ፣የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አበራ ቦጋለን ጨምሮ ሌሎችም የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።