የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ በትላንትናው ዕለት በዞኑ በሚገኙ መዋቅሮች የጀመረው የድህረ-ምርጫ ተግባራትንና የመደበኛ ሥራዎችን አፈፃፀም የድጋፍና ክትትል ሂደቱ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥለዋል።
የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ በትላንትናው ዕለት በዞኑ በሚገኙ መዋቅሮች የጀመረው የድህረ-ምርጫ ተግባራትንና የመደበኛ ሥራዎችን አፈፃፀም የድጋፍና ክትትል ሂደቱ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥለዋል።
በትላንትናው ዕለት በክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር የሚመራው የዞኑ የፓርቲ ኮሚቴ በዞኑ የሚገኙ የፓርቲ መዋቅሮች ያሉበትን ቁመና የመለየትና የፓርቲ መደበኛ ስራዎች እና የድህረ ምርጫ ስረዎች ያሉበት ደረጃ እያደረገ የነበረው ድጋፍና ክትትል ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥለዋል።
የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሕዝባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የፓርቲያችንን ስትራቴጂካዊ ግቦች ለማሳካት የሚያስችሉ የመደበኛና የድህረ-ምርጫ ሥራዎችን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል።
የድጋፍ ቡድኑ መሪና የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር በድጋፍና ክትትሉ ወቅት እንደገለፁት ብልፅግና ፓርቲ ከምርጫ ማግስት ጀምሮ ሙሉ ትኩረቱን ወደ ልማትና ወደ ሕዝብ አገልግሎት አዙሯል ሲሉ በመግለፅ ይህም ድጋፍና ክትትል የዝሁ አካል ነው ሲሉ ገልፀዋል።
እስካሁን በተደረገው ድጋፍና ክትትል ሰባት መዋቅሮች የታዩ ሲሆን በትላንትናው ዕለት ከሰአት በኋላ ጦራ ከተማ አስተዳደርና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች የታዩ ሲሆን በዛሬው ዕለት በጥዋቱ ክፍለ ግዜ ምዕራብ አዘርት በርበሬ ወረዳ እና ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳዎች የታዩ ሲሆን የድጋፍ ሂደቱ በሁሉም መዋቅር ተጠናክሮ ይቀጥላል።