የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ተሸላሚ ሆነ!
እንኳን ደስ አላችሁ ! እንኳን ደስ አለን!
የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ተሸላሚ ሆነ!
ሐምሌ 9/2018:- የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት "ከምርጫ ማግስት ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግሥት"በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም የማጠቃለያ መድረክ ላይ የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ተሸላሚ ሆኗል።
የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተሻሉ ስራዎችን በማከናወን በስልጤ ዞን ካሉ አጠቃላይ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤቶች የተሻለ አፈጻጸምን በማስመዝገብ የቤንዲንግ ማሽንና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሸልሟል።
ቅ/ጽ/ቤቱ ያስመዘገበው የተሻለ ውጤት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድምር ውጤት መሆኑን የገለጹት የጦራ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደኑር ኮሪ ለዚህ ውጤት እና ሽልማት መገኘት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል።
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ አለን